‹‹የሁሉ መጠጊያ›› . .

‹‹የሁሉ መጠጊያ›› . .
ፍጥረታት ሁሉ ከርሱ የሚፈልጉ እርሱ ግን ከማንም ምንም የማይፈልግ፣በራሱ ብቻ የተብቃቃ። (يُطۡعِمُ وَلَا يُطۡعَمُ)

‹‹የሚመግብ፣የማይመገብም ሲኾን፣›› [አልአንዓም፡14] ‹‹የሁሉ መጠጊያ›› . . አቀናባሪ ጌታ፣ያሻውን የሚፈጽም ፍጹማዊ ባለቤት። ‹‹የሁሉ መጠጊያ›› . . ልቦች ሁሉ ለጉዳዮቻቸውና ለችግሮቻቸው እርሱን ሲማጸኑ የሚሰጣቸውና የማይከለክላቸው። ሲለምኑት የሚሰማቸውና ችግራቸውን የሚያስወግድላቸው። ከርሱ የራቁት ሲጠሩት ሰምቷቸው ግንኙነቱን መላልሶ የሚቀጥልላቸው። የፈሩትንና የተሸበሩትን የሚያረጋጋና የሚያጽናና። በርሱ ላይ ተስፋ የጣሉትን ከግባቸው የሚያደርስ። አደጋ የተጋረጠባቸውን ነጻ የሚያወጣ። ባሮቹን በአምልኮው ሲተጉ ከፍ የሚያደርጋቸው።



Tags: