ነቢዩ ﷺ ከጌታቸው ባስተላለፉት መሰረት እንዲህ ብለዋል፦
‹‹አገልጋዮቼ ሆይ! በደልን በራሴ ላይ ክልክል አድርጌ በእናንተም ላይ ክልክል አድርጌያለሁና እርስ በርሳችሁ አትበዳደሉ። አገልጋዬቼ ሆይ! እኔ የመራሁት ካልሆነ በቀር ሁላችሁም የጠመማችሁ ናችሁ። ስለዚህ አመራርን ከኔ እሹ፤እኔም አመራሬን እሰጣችኋለሁ። አገልጋዬቼ ሆይ! እኔ የማበላችሁ ካልሆነ በቀር ሁላችሁም የተራባችሁ ናችሁና ሲሳይን ከኔ ለምኑ፤እኔም እመግባችኋለሁ። አገልጋዮቼ ሆይ! እኔ የማለብሰው ካልሆነ በቀር ሁላችሁም የታረዛችሁ ናችሁና ልብስን ከኔ ለምኑ፤እኔ አለብሳችኋለሁና። አገልጋዮቼ ሆይ! ቀንም ሆነ ማታ ኃጢኣትን ትሰራላችሁ፤እኔ ኃጢኣቶችንም በሙሉ ይቅር የምል ነኝና ይቅርታን ከኔ ለምኑ፤እኔ ይቅር እላችኋለሁና። አገልጋዮቼ ሆይ! ልትጎዱኝ አይቻላችሁም፤ ልትጠቅሙኝም አይቻላችሁም። አገልጋዮቼ ሆይ! ከናንተ የቀደሙትና የሚከተሉት (ትውልዶች)፣ሰዎቻችሁና ጅኖቻችሁ በመካከላችሁ ካለውና ልቡ እጅግ የጠራ በሆነው በኩል ብትሰባሰቡ እንኳ በግዛቴ ላይ አንዳችም ነገር አትጨምሩም። አገልጋዮቼ ሆይ! ከናንተ የቀደሙትም ሆኑ የሚከተሉት፣ሰዎቻችሁም ሆኑ ጅኖቻችሁ፣ከመካከላችሁ እጅግ የከፋ ልብ ካለው በኩል ብትተባበሩ ከግዛቴ ቅንጣት አትቀንሱም። አገልጋዮቼ ሆይ! ከናንተ የቀደሙትም ሆኑ የሚከተሉት፣ ሰዎቻችሁና ጅኖቻችሁ፣በአንድ አደባባይና ሥፍራ ሆነው ቢለምኑኝና ለያንዳንዳቸው የሚፈልገውን ሁሉ ብሰጥ መርፌ ከውቅያኖስ ብትገባ የምታጎድለውን ያህል እንኳ እኔ ዘንድ ካለው ላይ አይጎድልብኝም።
አገልጋዮቼ ሆይ! ለናንተ እኔ ዘንድ የምቆጥርላችሁና ከኔ ምንዳ የሚያሰጧችሁ ሥራዎቻችሁ እንጂ ሌላ አይደለም፤ስለዚህ ጥሩ ያገኘ ሰው አላህን ያመስግን፤ከዚህ ውጪ ያገኘ ማንንም ሳይሆን ራሱን ይውቀስ።››
(በሙስሊም የተዘገበ)
አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦
(يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ أَنتُمُ ٱلۡفُقَرَآءُ إِلَى ٱللَّهِۖ وَٱللَّهُ هُوَ ٱلۡغَنِيُّ ٱلۡحَمِيدُ ١٥)
‹‹እላንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁል ጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፤አላህም እርሱ ተብቃቂው፣ምስጉኑ ነው።››
]ፋጢር፡15[
‹‹አገልጋዮቼ ሆይ! ለናንተ እኔ ዘንድ የምቆጥርላችሁና ከኔ ምንዳ የሚያሰጧችሁ ሥራዎቻችሁ እንጂ ሌላ አይደለም፤ስለዚህ ጥሩ ያገኘ ሰው አላህን ያመስግን፤ከዚህ ውጪ ያገኘ ማንንም ሳይሆን ራሱን ይውቀስ።››
(በሙስሊም የተዘገበ)
የአላህን ትእዛዛት ጠብቅ እርሱ ይጠብቅሃልና፦
ከዐብዱላህ ብን ዐብባስ (ረዐ) በተላለፈው መሰረት ከዕለታት አንድ ቀን ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ኋላ (ተፈናጥቼ) እያለሁ፣እንዲህ አሉኝ ብለዋል፦
‹‹አንተ ብላቴና ሆይ! ጥቂት ቃላትን (ትምህርቶችን) አስተምርሃለሁ፦ ትእዛዛቱን በመፈጸም የአላህን መመሪያ ጠብቅ፣እርሱም ይጠብቀሃልና። ትእዛዛቱን በመፈጸም የአላህን መመሪያ ጠብቅ፣(በጥበቃው በረድኤቱና በዕውቀቱ የትም ቦታ) ካንተ ጋር ሆኖ ከፈት ለፊትህ ታገኘዋለህና። ስትለምን አላህን ብቻ ለምን፤እርዳታ ስትፈልግ በአላህ ብቻ ታገዝ። ሕዝቦች ሁሉ አንዳች ነገር ሊጠቅሙህ አንድ ላይ ቢሰባሰቡ፣አላህ ቀድሞውኑ ወስኖ ከጻፈልህ ውጭ ምንም አይጠቅሙህም። በአንዳች ነገር ሊጎዱህ አንድ ላይ ቢሰባሰቡ፣አላህ ቀድሞውኑ ወስኖ ከጻፈብህ ውጭ ምንም አይጎዱህም። ውሳኔው ተላልፎ መዝገቡ ተዘግቷልና። ››
(በትርምዚ የተዘገበ)
አላህ ﷻ
አላህን ይበልጥ የሚያውቅ አላህን ይበልጥ ይፈራዋል።