የአምላክ ትርጉም ፦

የአምላክ ትርጉም ፦
‹‹ላ እላሀ እልላሏህ››

ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ የለም ፦

የጠራ ቃለ ተውሒድ ነው። አላህ በአገልጋዮቹ ላይ ግዴታ አድርጎ ከደነገጋቸው ግዴታዎች ሁሉ ታላቁ ነው። ተውሒድ ሃይማኖት ውስጥ የሚይዘው ስፍራ ራስ ከሰው አካል የሚይዘውን ስፍራ ነው።

የአምላክ ትርጉም ፦

አምላክ (እላህ) ፦

የሚያመልኩትና የሚታዘዙት፣አምልኮት የሚገባው።

(وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا)

‹አላህንም ተገዙ፤በርሱም ምንንም አታጋሩ፤››

[አልኒሳእ፡36]

የ‹‹ላ እላሀ እልላሏህ›› (ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ የለም) ትርጉም ፦

ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክና አምልኮት የሚገባው ሌላ አምላክ የለም፣ማለት ነው።

ቃለ ተውሒድ ከሁለት መሠረታዊ ማእዘኖች የተገኘ ነው ፦

አንደኛው - እውነተኛ አምላክነትን ከአላህ በስተቀር ከሌላው ሁሉ ማስተባበል።

ሁለተኛ - እውነተኛ አምላክነትን ለአላህ ﷻ ብቻ ማረጋገጥ ።



Tags: